የኮንስትራክሽን ሚኒስትር ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሐመድ መልዕክት

የኮንስትራክሽን ሚኒስትር ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሐመድ መልዕክት

ሀገራችን ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ድህነት በዘላቂነት ተላቅቃ በአጭር ጊዜ ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ እንድትሰለፍና ቀጣይነት ያለው ዘላቂ ዕድገትና ብልጽግናን ለማምጣት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ልማት ስኬት የማይተካ ሚና አለው፡፡ በማደግ ላይ ያለውን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ቀጣይነት ለማረጋገጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ በስፋት ሲከናወኑ የቆዩት ሠፋፊ የመሠረተ ልማትና የህንፃ ግንባታ ስራዎች የዚህ እውነታ ማሳያዎች ናቸው፡፡

 

በቀጣይም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ዘርፍ በፍጥነት ማደግ ተከትሎ ራሱን ችሎ የተቋቋመው የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የመሪነት ሚናውን በአግባቡ ለመወጣትና የዘርፉ ተዋናዮች የኢንዱስትሪውን ዕድገት ወደ ሚፈለገው ደረጃ እንዲያደርሱት ለማድረግ በየጊዜው እያደገ የሚሄድ አቅምን ለመፍጠር እየሠራ ይገኛል፡፡

ስለሆነም በሀገሪቱ ቀጣይነት ያለው ልማትን በማረጋገጥ ሂደት በላቀ ደረጃ ውጤት እንዲመዘገብ ለማድረግ፣ ለግንባታ ሥራዎች አስፈላጊውን ድጋፍ በመስጠት ረገድ የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት ብቁና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የመፍጠር ራዕይን እውን ለማድረግ በመላ ሀገሪቱ ለማስፈፀም ያቀድናቸው የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሰረተ ልማቶች ማለትም የመንገድ፣ የሕንጻ፣ የኃይል፣ የውሃ ልማት ወዘተ. የኮንስትራክሽን ዘርፎች የሚመሩበት ሥርዓት ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሁም በልማታዊ ፖለቲካል ኢኮኖሚ የተቃኙ እንዲሆኑ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ ናቸው፡፡በመሆኑም የተያዘውን ዕቅድ ውጤታማ ለማድረግ የዜጎችን ተሣትፎና ወደተግባር ለማምራት የሚያስችል እምነትን በመያዝ ተሣትፎ ማድረግን የሚጠይቅ ስለሆነ በዘርፉ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያላቸው አካላትና ባለድርሻዎች እንዲሁም መላው ህብረተሰብ በአፈፃፀም ላይ እያጋጠሙ ባሉ ዋና ዋና ችግሮችና ቀጣይ ትኩረትን በሚሹ ጉዳዮች ላይ ግልጽነትን በመያዝ ለኪራይ ሰብሳቢነት የተመቹ ሁኔታዎችን በማዳከም የልማታዊነት አመለካከትና ተግባራት እንዲያብቡና እየጎለበቱ እንዲሄዱ ለማድረግና የምንናፍቀውን ለውጥ ለማምጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከጎናችን በመሰለፍ የጋራ ትግል እንዲያደርጉ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ፡፡

                                                                 አመሰግናለሁ!