ለሙያ ፈቃድ አዲስ ተመዝጋቢዎች ለሙያ ፈቃድ አዲስ ተመዝጋቢዎች

ሀ/ የሙያ ፈቃድ በኮንስትራክሽን /በዲዛይን አዲስ ለማውጣት መቅረብ ያለባቸው መረጃዎች፡

 1. የትምህርት ማስረጃ (ዲግሪ፣ ከፍተኛ ዲፕሎማ፣ ዲፕሎማ ወይንም ሠርተፍኬት) ዋናውንና አንድ አንድ ፎቶ ኮፒ፣ እንደዚሁም የወሰዱትን የኮርሶች ዝርዝርና ውጤት የሚገልጽ ትራንስክሪፕት (Student Copy) ዋናውንና አንዳንድ ፎቶ ኮፒ፣

 

 1. ጊዜያዊ ዲፕሎማ (Temporary Diploma) ከምረቃ ጊዜ አንስቶ 6 ዓመት ያለፈው ከሆነ ዋናውን ዲፕሎማ ማቅረብ ግዴታ ነው፡፡ ይሀንን ማቅረብ ካልቻሉ  ከተመረቁበት ተቋም ዋናው ዲፕሎማ በመዘጋጀት ላይ መሆኑን የሚገልጽ በቅርብ ጊዜ የተጻፈ  (ስድስት ወር ያላለፈው) ደብዳቤ፣ እንደዚሁም  የወጪ መጋራት ክፍያ (Cost Sharing) ከፍለው ማጠናቀቃቸውን የሚያረጋግጥ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የተጻፈ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 • ከውጭ አገር የትምህርት ተቋማት የሚቀርቡ የትምህርት ማስረጃዎች የአቻ ግምት ከትምህርት ሚኒስቴር ሊያቀርቡ ይገባል፡፡
 1. በቅርብ ጊዜ የተነሱት፣ ሦስት በአራት ሳይዝ ያለው ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ፣
 2. የሥራ ልምድ ማስረጃ ካለ ዋናውንና አንዳንድ ፎቶ ኮፒ፣
 • የሚያቀርቡት የስራ ልምድ ማስረጃ ከምረቃ በኋላ ሊሆን ይገባል፡፡
 • የሚያቀርቡት የሥራ ልምድ ማስረጃ የተሟላ ሊሆን ይገባል፡፡ ማለትም ፡-የደብዳቤ ቁጥር፣ ቀን፣ የሥራ መደብ፣ ደመወዝ፣ የገቢ ግብር የተከፈለ ስለመሆኑ፣ የሠሩበት ጊዜ (ከ….እስከ….)፣ ደብዳቤውን የፈረመው ኃላፊ  የሥም ቲተር እና  የድርጅቱ ማህተም
 • የሚያቀርቡት የሥራ ልምድ ማስረጃ በአማርኛ ወይም በእንግሊዝኛ ከሆነ ተቀባይነት አለው፡፡ ከዚህ ውጭ ከሆነ የትርጉም ሥራ ፈቃድ ባለው ድርጅት አስተርጉመው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 • የሚያቀርቡት የሥራ ልምድ ማስረጃ ከግል ድርጅቶች ወይንም መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ከሆነ የገቢ ግብር ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን  የተከፈለ ሰለመሆኑ ከሠሩበት ተቋም መረጃ ማቅረብ፣ እንደዚሁም የሠሩበት ድርጅት ወርሃዊ የደመወዝ መክፈያ መረጃ (Pay Roll) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ከውጭ አገር ለሚቀርቡ የሥራ ልምድ ማስረጃዎች ከኤንባሲዎችና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማረጋገጫ (autontication) መቅረብ አለበት፡፡

 

 1. የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ካርድ ዋናውንና እንድ ፎቶ ኮፒ፣
 • የታደሰ መንጃ ፍቃድ ወይም የግብር ከፋይ መለያ ካርድ (TIN) ዋናውንና አንድ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይቻላል፡፡ 
 1. ከሚኒስቴር መ/ቤቱ የሚሰጣቸውን የማመልከቻ ቅጽ በአግባቡና በጥንቃቄ ሞልቶ መፈረም
 2. የአገልግሎት ክፍያ መክፈል፣

 

 

Pages: 1  2  3  4  5