ተግባራትና ኃላፊነቶች ተግባራትና ኃላፊነቶች

 

ሀ) ለሌሎች አካላት በሕግ የተሰጠው ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ የኮንስትራክሽን ሥራዎችን ደረጃ ያወጣል፣ መከበራቸውን ይከታተላል፤

ለ) በዓለም አቀፍ ደረጃ የተወዳዳሪነት ብቃት ያለው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለመገንባት የሚያስችሉ የተመቻቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ያደርጋል፤

ሐ) በፌደራል መንግሥት በጀት ለሚሠሩ ሕንፃዎች ዲዛይኖችና የግንባታ ውሎች እንዲዘጋጁ በማድረግና የግንባታ ሥራዎችን በመቆጣጠር ረገድ አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል፣

መ) በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚሰማሩ መሐንዲሶችና አርክቴክቶችን ይመዘግባል፣ የሙያ ችሎታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፤ የሥራ ተቋራጮችንና የአማካሪዎችን ደረጃ ይወስናል፤ ከአንድ በላይ በሆኑ ክልሎች ውስጥ መሥራት ለሚችሉ የሥራ ተቋራጮችና አማካሪዎች የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፤

ሠ) አገር በቀል የኮንስትራክሽን ድርጅቶችን ብቃትና ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ስትራቴጂ ይቀይሳል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤

ረ) በአገር ውስጥ የሚመረቱ የኮንስትራክሽን ዕቃዎችን ዓይነትና ጥራት ለማሻሻል የሚረዳ ምርምር ያካሂዳል፤

ሰ) የህንጻ ኮድና ስታንዳርዶች በከተሞች ተፈጻሚ እንዲሆኑ ተገቢው አደረጃጀት፣ አሠራርና የሰው ሃይል አቅም እንዲፈጠር ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን ይደግፋል፣ ይከታተላል፡፡

2/ በሥራ ላይ ባሉ የሌሎች ሕጎች ድንጋጌዎች ኮንስትራክሽንን በሚመለከት ለከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ተሰጥተው የነበሩ ሥልጣንና ተግባሮች በዚህ አዋጅ ለኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ተሰጥተዋል፡፡