ታሪካዊ ኣመሰራረት ታሪካዊ ኣመሰራረት

በአገሪቱ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ከፍተኛና ዘርፈ ብዙ የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ አስፈጻሚ ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት በየጊዜው እየፈተሹ አዳዲስ አደረጃጀቶችንና አሰራሮችን መፍጠርና ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህም መሠረት በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ያለው አገራዊ ፍላጎት እየጨመረ መምጣትና የሚጠበቀው የአፈጻጸም አድማስ እና ዘመኑ የሚጠይቀውን የኢንዱስትሪውን አመራርና ልዩ ባህርይ ከአገሪቱ ፈጣን ዕድገት ጋር ማቀናጀት ወሳኝ ስትራቴጂካዊ ተግባር ነው፡፡

ከዚህ አኳያ ከአገራዊና ዓለም-አቀፋዊ ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውንና የሚኖረውን ግንኙነት፣ እንዲሁም የሙያ ዘርፉና ቴክኖሎጂው በሚጠይቀው መጠን ምላሽ ለመስጠትና በቀጣይነትም ኢንደስትሪው በአገሪቱ የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ የጎላ ሚና እንዲኖረው በማስፈለጉ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር 916/2008 ዓ.ም ተቋቁሟል፡፡

መንግስት በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ያሉትን ዘርፈ ብዙ ተግባራት አግባብነት ባለው ሁኔታ ለመምራትና የአገሪቱን የልማት እንቅስቃሴ ለማፋጠን እንዲረዳ ቁልፍ ተግባራትን በመለየት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲ አውጥቷል፡፡ በመሆኑም በኢንዱስትሪው ያሉትን ተግባራት በማከናወን በፖሊሲውና በመንግስት የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት በተሟላና በተደራጀ መልኩ ለማከናወን እንዲቻል አደረጃጀቱን አሰራሩን መቅረጽ አስፈላጊ በመሆኑ፣ በዚህ ሰነድ የተቀረጸው የተቋማዊ አደረጃጀት ቀርቧል፡፡

በዚህ መሰረት፣

  • የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ስልጣንና ተግባር እንዲሁም ራዕይ፣
  • በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ላይ በቀረቡ ፖሊሲ ጥናቶችና በዘርፉ ላይ ተቀመጡ የልማትና የለውጥ አቅጣጫዎች፣
  • በተለያዩ ወቅቶች የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በተናጠልም ሆነ በጋራ የሌላ መሥሪያ ቤት አካል ሆኖ የነበረበትን አደረጃጀትና አፈጻፀም በመፈተሽና ጠንካራ ጎኖችን ከግንዛቤ በማስገባት፣
  • ዘመኑ በኢንደስትሪው አመራረር የደረሰበትን አተገባበር፣ከልማት አጋሮቻችንና በአገራችን ውስጥ ከተሰማሩ የኢንደስትሪው ተዋናዮችን ለመምራትና ለመናበብ የሚያስችሉ አካሄዶችን